ካንተ ውጪ ክብር /3/
ክብሬ አንተ ነህ
ቢፈለግ አይገኝ ክብር በውበት
ቢፈለግ አይገኝ ክብር በእውቀት
ቢፈለግ አይገኝ ክብር በሹመት
ቢፈለግ አይገኝ ክብር በኩራት
ካንተ ውጪ ክብር /3/
ክብሬ አንተ ነህ
እንደጠዋት ጤዛ እንደሚጠፋው
እንዲሁ እኮ ነው ከሰው የሆነው
ዛሬ ሆ እያለ ከፍ ከፍ ያረገው
ሆ ብሎ ይነሳል ነገን ሊያዋርደው
ያለምንም ከፍ ከፍ የሚያደርግ
በሰማይም በምድርም እግዚያብሔር
ካንተ ውጪ ክብር /3/
ክብሬ አንተ ነህ
ከቶ ኣትፈልገው ለነፍስህ ቢያምር
የጊዜያዊውን የዚህን ኣለም ክብር
የአምላክህን ቃል ኑር እንጂ ሳትንቅ
ክብር ይሆንሐል እርሱን ስታከብር
የሚያከብሩኝን አከብራለሁ
የሚንቁኝ ግን ይናቃሉ
ያለው በዙፋኑ ነው /4/
