ኧረ እንዴት ባለ ፍቅሩ ወደደኝ
አንድ እቅድ እንኳን ከኔ ሳይኖረኝ
ምንም ሳልሰራ በሰጠኝ ፀጋ
እንዲሁ ወደደቃ ከፈለልኝ ዋጋ
በጨለማ ህይወት ተስፋ በሌለበት
ልቤን በሰበረው ሸንጐ በቆምኩበት
ሃጥያት የሌለበት ድንጋዩን ይወርውር
ብሎ ገለበጠው የመሞቴን ነገር
ህይወቴን ያደሰው ኢየሱስ
የነፍስ የስጋዬ ፈውስ
አዳኝ ኢየሱስ የሰላም ጌታ
አከብረዋለሁ ጠዋት ማታ
በርቺ ልጄ ከቶ አትሞችም
ከሳሾችሽም ከዚህ የሉም
ያለቃ ጌታ እርሱ ብቻ
እንቆቅልሼን ሁሉ የፈታ
የተናቀውን የሚያከብር
ቀንበርን የሚሰብር
እጅግ ድንቅ ፍቅር ያለው
ምሮኛልና አከብረዋለሁ
ድንጋዩን በእኔ ላይ ሲጥሉ
ትሙት በቃ ሰዎች ቢሉ
ጻድቅ ፈራጅ ለካ አለ
እዳዬን ሁሉ የከፈለ
የፍቅሩ ጥልቀት ገረመኝ
በሰላሜ ኑሪ ሲነኝ
የፍቅሩ ጥልቀት ገረመኝ
በሰላሜ ኑሪ ሲነኝ
