የኛ ሰላም

80

አሁንም አንተው ነህ የኛ ሰላም
ና ለልጆህ ና አታደላም
አሁንም ኢየሱስ ያለም ሰላም
ብቸኛው አንተ ነህ የለም ሌላም

ሁልጊዜ አይረበሽ አይሰጋ አረፈ ከጐኑ የቆምክለት
የታደለ ምስጉን ህዝብ ነው ኢየሱሴ ሰላም የሆንክለት
በነፍሱ ምስክሩ ሞልቶ ይበልህ እንጂ የሰላም አለቃ
ታዲያማ ፃድቅ የት ይሄዳል ፍለጋው በአንተ አርፎ ከበቃ

የስልጣናት የመኳንንቱ የነገስታት ምክክራቸው
አይደለም መፍትሔ የሚሆን ለኛ የሰላማችንም መገኛ
አንተው ነህ ኢየሱስ አንተው ነህ ዛሬም ቢሆን ነገም ለዘለአለም
የመንፈስ እርካታ ፀጥታ የምታላብስ በደስታ

የሰዎች ፍቃድ የሞላበት መንፈስህ ፍፁም የሌለበት
ዓለም ለዓለም እንደምትሰጠው አይደለም ያንተ ሰላም በእውነት
ዘወትር አይምሮን የሚያልፍ አይደርቅም ፀጋው ነው ለዓለም
ከምንጭህ ተጠጋን ኢየሱስ የአንተን ሰላም የሚተካው የለም

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top