የዘገየ መሰሎኝ ነበር ስለቴ
ደረሰልኝ በረከት ሞላ ቤቴ
ሳወራው ለሌላ እንድሆን ምሳሌ
እመኑኝ ቀዳሚ የለው አባቴ
ያቀድኩት ሲሞላ የልቤ
ምኞቴ ሲሳካ እንደሐሳቤ
ተደነቅኩ ተገረምኩ በጌታ
ችግሬን በቶሎ ሲፈታ
ምን ልበለው ጌታ ኢየሱሴን
ምስጋና ልሰዋ ከነፍሴ
የዘገየ መሰሎኝ.………….
መስሎኝ ነበር የተረሳሁ እኔ
እርሱ ባይደርስልኝ መድህኔ
ውለታውን አረሳም ኧረ እኔ
የሞተልኝ በሕይወት ዘመኔ
ምን ልበለው ጌታ ኢየሱሴን
ምስጋና ልሰዋ ከነፍሴ
ለካ አለው ጊዜ የሚደርስበት
ምስኪኑን የሚጐበኝበት
ያለፈውን መከራ አስረስቶ
ልቤንም በደስታ ሞልቶ
ምን ልበለው ጌታ ኢየሱሴን
ምስጋና ልሰዋ ከነፍሴ
ልዩ ነው እርሱ ልዩ /2/ ልዩ ነው ጌታ ልዩ
ፍቅር ነው እርሱ ፍቅር /2/ ፍቅር ነው ጌታ
