ሃያል ነው እግዚአብሔር ግርማው
ለዘለአለም የሚያስፈራ
ጥበቡ ድንቅ ነው ግሩም የእርሱ ስራ /2/
ሰማይና ምድር የእርሱ ስራ ናቸው
እራሱ በእጁ ፈጥሮ የሰራቸው
ሃያል ነው ድንቅ ነው እርሱ
ያስፈራል ግርማ ሞገሱ
ያክብሩት ፍጥረቱ ሁሉ
ለክብሩ ለፍቅሩ ሲሉ
እንስሳት አእዋፍ ለርሱ ይዘምራሉ
ክዋክብት ጨረቃ ክብሩን ያወራሉ
ሃያል ነው ድንቅ ነው እርሱ
ያስፈራል ግርማ ሞገሱ
ያክብሩት ፍጥረቱ ሁሉ
ለክብሩ ለፍቅሩ ሲሉ
ከነገስታት በላይ ሐይል አለው ዙፋኑ
ከቶ አያቋርጥም ንግስና ዘመኑ
ይኖራል ዘለአለም እርሱ
ያስፈራል ግርማ ሞገሱ
ይስገዱ ፍጥርት ሁሉ
ለክብሩ ለፍቅሩ ሲሉ
በፍቅር ይገዛል ልዝብ ነው ቀንበሩ
አምኖ ለሚያንኳኳ ይከፈታል በሩ
ታጋሽ ነው የዋህ ነው እርሱ
ያፀናናል ቅዱስ መንፈሱ
ይስገዱ ፍጥረት ሁሉ
ለክብሩ ለፍቅሩ ሲሉ
በጥበቡ የሰራ ሁሉን በየመልኩ
ልቦና የሰጠ እርሱን እንዲያመልኩ
ድንቅ ነው ፍጥረት ስራው
ጥበቡ ወደር የለው
ይስገዱ ፍጥረት ሁሉ
ለክብሩ ለፍቅሩ ሲሉ
መቃብር ፈንቅሎ ሙታን የሚያስነሳ
የተናገረውን ቃል የማይረሳ
ድንቅ ነው ፍጥረት ስራው
ጥበቡ ወደር የለው
ይስገዱ ፍጥረት ሁሉ
ለክብሩ ለፍቅሩ ሲሉ
