ፍቅር ነህ ጌታ

84

ፍቅር ነህ ጌታ ፍቅር ነህ
ፍቅር ነህ ኢየሱስ ፍቅር ነህ ውለታህ
የበዛ ታማኝ ነህ
ውለታህ የበዛ ታማኝ ኣምላክ ነህ /2/

በዙፋንህ ላይ ሆነህ አለምን ታያለህ
የዘለአለም አባት ቅዱስ አምላክ ነህ
በክፉ ስራችን ብናሳዝንህም
ሁሉንም ታያለህ ምንም አትቸኩልም

ልባችን በማየት የምትፈርድ አንተ ነህ
ክብር ይገባሃል ለሃያሉ ስምህ
በፍቅር አይኖችህ ትመለከታለህ
ፍጥረታትን ሁሉ ትጠብቀዋለህ

እንዳተ ያለ ጌታ ከወዴት ይገኛል
በእውነት ልዩ ነህ ሁሉ ይቻልሐል
ውለታህ ብዙ ነው ምን እንልሃለን
ዘለአለማዊ ንጉስ ንገስ እንልሃለን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top