እንዘምራለን

85

እንዘምራለን በክብር እናቀርባለን ምስጋና
ማዕበሉን ከፍሎ አሻግሮናል ጠላታችን ወድቋል .
እንደርሳለን በደስታ ወደ ተስፋይቱ ምደር
በጋራ አብረን እንኖራለን ቃል ገብቷል እግዚኣብሔር

ይዘን እንቀርባለን ምስጋና ካምላካችን ደጅ ውዳሴ
በዋዛ አልጣለንም ጌታችን በጠላቶች እጅ ምስጋና
ዝማሬአችን ይድረስ ከሰማይ እንደ ኣሮን ሽቶ ውዳሴ
እንደ አምላክ ያለ በፍፁም አይገቃኝ ከቶ ምስጋና

የሚከሰን ጠላት በባህር ወድቋል ከኋላችን ምስጋና
የልባችን ደስታ ይገለጥ ይድመቅ ዝማሬአችን ውዳሴ
ባህር ከፍሎ ሚያቆም በተአምር ህዝቡን አሻጋሪ ምስጋና
ከኛጋራ ያለ አምላክ ይበልጣል የዓለም ፈጣሪ ውዳሴ

ጥቂት ቢያደክመንም ግለቱ ተራራ ዳገቱ ምስጋና
እግዚአብሔር ነውና አቅማችን የመጣው ብርታቱ ውዳሴ
ፍፁም አልራበንም በጭራሽ አልጠማንም ውሃ ውዳሴ
ዝለን አልወደቅንም በፍፁም በሲና በረሃ ውዳሴ

እንደጠላት ሃሳብ ምኞት ቢሆንማ ሁሉ ምስጋና
ጭራሽ ጠፍተን ነበር በጠላት
ገብተን ከገደሉ ውዳሴ
ኣያዋጣም እና በፍፁም በራስ መመካቱ ምስጋና
እግዚአብሔርን ትቶ አይሆንም
ጉልበት ማመን ከንቱ ውዳሴ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top