ይወዳል እግ/ር ምስጋና ይወዳልና
ማደሪያ ዙፋኑን እናብዛ ዛሬ እደገና
ዛሬ እንደገና ይብዛ እንደገና /2/
አይነስ እንስጠው ሳንቆጥብ ምስጋና
እግ/ር ምህረቱ በዝቶልናልና
ተፈታሁኝ ያለ ምላሹን ያምጣለት
አይፈር ዝም አይበል ውለታው ያለበት /2/
ጌታ ብዘምር እኔስ በአንተ አላፍር
ሳላቆም ምስጋና እሰዋለሁ ገና /2/
እንደገና/6/
አንድ ሁለት አይባል እግ/ር ወለታው
በትላንት አይበቃም ዛሬም ኤልሻዳይ ነው
ከልብ ይፍለቅና ምስጋና ይብዛለት
ደግሞ ይውደደው እንጂ የምን ዝም ማለት / ክብሬን እጥልለት
አምልኮ ምስጋና ሙገሳ ለክብሩ
ጠዋት ማታ ይብዛ ጌታ ለአሰራሩ
እሱ ይወዳልና ከእሱ ለሱ ክብር
ትንሹም ትልቁም ምስጋና ይዘምር / ይደርድር
