ሰማይን በብልሃት ጌታ አንተ ሰርተሃል
ምድርን በውሃ ላይ እንዲሁ አፅንተሃል
ብቻህን ታላላቅ ብርሃናት የሰራህ /2/
ግሩም ነህ /4/
ሥራህ ረቂቅ ነው ጥበብም የሞላህ
ለጨረቃና ክዋክብት ሌሊቱን ያስገዛህ
ፀሃይንም ደግሞ በቀን ላይ ሾመሃል
ግሩም ነህ /4/
የእጆችህን ስራ ጌታ እኔ አደንቃለሁ
መንፈሳዊ ቅኔን ለአንተ እቀኛለሁ
እቀኛለሁ /4/
አምላክ ያማልክቶች አምላክ
አምላክ አምላክ ነህ
ጌታ የጌቶች ጌታ
ጌታ ጌታነህ
ጌታ ገዢ
ገዢ የፍጥረታት ገዢ
ገዢ ገዢ ነህ
ገዢ ፍቅር
ፍቅር እውነተኛ አፍቃሪ /2/
እውነትም ፍቅር ኢየሱስ ነህ
እውነትም ወዳጅ ኢየሱስ ነህ
