ቅዱስ እግ/ር

93

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ሃያል ሃያል ሃያል እግዚኣብሔር
ልኡል ልኡል ልኡል እግዚአብሔር

ሰማይና ምድርን በቃልህ ያፀናህ
ለመንግስትህ አልፋ ኦሜጋ የሌለህ
በክብር በግርማህ እጅግ ከፍ ከፍ ያልክ
አንተ ነህ እግዚአብሔር እኛ የምናመልክህ

ሱራፌል ኪሩቤል የሚያመሰግኑህ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሚያመልኩህ
በክብር በግርማህ ደምቀህ የምትታይ
አንተ ነህ አዶናይ እኛ የምንሰግድልህ

መላዕክት ግርማህን የሚያሞግሱልህ
ፃድቃን በዝማሬ ክበር ንገስ ሚሉህ
በሰማይ በምድር ነግሰህ የምትኖር
የአማልእክት አምላክ አንተ ነህ እግዚአብሔር

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top