ኦ ሃይልነትህ

93

ኦ ሃያልነትህ ወደር የሌለው ነው
ፍቅርን በመለገስ ሁሌም ገናና ነው/2/

ገናና ነው ገናና ገናና ነው

በአምሳያህ አድርገህ ሰውን የፈጠርክው
በክብር ምስጋና ዘውድም ከልለኸው
ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳንሰኸው
በእጆችህ ስራ ሁሉ ላይም ሾምኸው /2/

የጠላትህን መንደር ሜዳውን ኣፈረስክ
አህዛብን ገስጽህ ዘንጉን አጠፋህ
የሞተውን እሬሳ በቃልህ አስነሳህ
በክብር በምስጋና ሁልጊዜ ላክብርህ /2/

ምድር ብትለኝም ተስፋ ቢስ ብቸኛ
ጓደኛ አለቃ እኔ ፈፅሞ የማይተኛ
የዘለአለም ጌታ ህይወት የሚሆነኝ
መስቀል ተደግፎ ለኔ ሲል ሞተልኝ /2/

ችግረኛ አይቶ ዝም አይልም ልብህ
በሃዜኔ ጊዜ ፈጥነህ ትደርሳለህ
ባንተ ሃያልነት ምን ያጣሁት አለ
ጌታዬና አምላኬ ፍቅርህ ውስጤ አለ /2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top