አቅጣጫዬን ስቼ በጠፋሁኝ ጊዜ
መላቅጡ ጠፍቶኝ ሳለሁ በትካዜ
አንተ ነህ የረዳኸኝ አንተ ነህ የመራኸኝ
የመኖርህ ትርጉም ይህ ነው ብለህ ያልኸኝ
ክበር የኔ ጌታ ይህን ላረክልኝ
ብፈልግ አጡሁኝ እንዳንተ የሚሆነኝ
ሌላ ምን እላለሁ ጌታ ክበርልኝ
ምስጋናዬ ይኸው አንተን ከፍ ያርግልኝ
ማንነትህን ሳላውቅ ካንተ ብሸሸግም
አንተን አስከፍቼ ትዕዛዝህን ብጥስም
እጅህን ዘርግተህ ጠርተኽኝ በስሜ
ገዝቼሃለሁኝ አልከኝ በክቡሩ ደሜ
መከራው በዝቶብኝ ኖርኩት አይኖሩት
ዝቅተኛ ሆኜ ላቆይ ብል ሕይወቴን
መረሳቴን አይቶ ታሪኬን ለውጧል
የመከራዬን እጥፍ በረከት ሞለቶኛል
በድቅድቅ ጨለማ በሌለበት ብርሃን
በትካዜ ሕይወት በችግርም ስሆን
ረዳት የሚሆነኝ በፍጹም አጣሁኝ
አንተ ግን አግኝተህ በብርሃን መራኸኝ
ክበርልኝ /3/ ጌታ
ክበርልኝ /3/ፈዋሽ
ክበርልኝ /4/
ምሥጋና ለአንተ ይገባሃልና
እልልታ ለአንተ ይገባሃልና
ሽብሸባ ለአንተ ይገባሃልና
ጭብጨባ ለአንተ ይገባሃልና
ሙገሳ ለአንተ ይገባሃልና
አምልኮ ለአንተ ይገባሃልና
