ይኸው በመዝሙሬ

96

በቃ አበቃለት ተብሎ ተስፋ የተቆረጠበት
በጌታ ሲጎበኝ ሲወሳ ሲያገኝ ሕይወት እስትንፋስን
ታሪኩ ምዕራፉ ሲለወጥ ጥንት የነበረበት ዝናው
ምሥጋናን ዝማሬ ለጌታ ይኸው ዛሬ አፈሰሰው

በምህረትህ ጎበኘኸኝ ባሪያህን አዕብከኝ
ዛሬስ ቀን ወጣልኝ እንዲህ አከበርከኝ
ከውድቀት አንስተህ የክብር ዕቃ አድርገህ
ለአንተ እንድዘምር በመዝሙር ባርከህ

ይኸው በመዝሙሬ /2/
ይኸው በአምልኮዬ /2/
ከፍ በል ጌታዬ

በዓለም ውጥንቅጥ ውስጥ ተይዛ ስትጨነቅ እንዳልነበረ
አንድ ቀን ኢየሱስ ደረሰና የነፍሴን ታሪኳን ቀየረ
ነፍሴም አቅቷታል ዝምታ ለእርሱ ትለዋለች ምሥጋና

ፍጹም ማይረሳ ውለታ ኢየሱስ ውሎላታልና

ላረክልኝ ብዙ ውለታ ምን አለኝ ምን እሰጥሃለሁ
አንተው በሰጠኸኝ ልሳኔ ዝማሬን እቀኝልሃለሁ
ባይመጥንም ላንተ ውለታ ይሻላል እንዲያው ከዝምታ
ይድረስህ ይኸው መስዋቴ ከፍበል ውዱ የእኔ ጌታ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top