ኢየሱስ ገናና ነው

97

ሥራዬን ሁሉ እግ/ር ሠራ
ድቅድቅ ሕይወቴ ዛሬ በሱ በራ /2/
ክብርን በዜማ እቀኝለታለሁ
ካሳ እንኳን ባይሆን ሁሌ እዘምራለሁ እወድሳለሁ

ኢየሱስ ገናና ነው ገናና
እንስጠው ምስጋና በዜማ
ትላንት ዛሬ ከጥንት ኃይለኛ
ታሪክን የሠራ ዝነኛ

አላውቅም ነበር መቅደስ ገብቼ
ለብዙ ዘመን በደጅ ተኝቼ
በውጭ ተኝቼ
በሃሳቤ የሌለ ቀድሞ ያላሰብኩት
በቅቶሃላ አለኝ ስሙን ከፍ አድርጉት
ገናና ነህ በሉት

በምድረ በዳ ልጄ ተጠምቶ
ሞተብኝ ብዬ ልቤ እጅግ ፈርቶ /2/
ሳላየው አየኝ ከላይ መድህኔ
አረሰረሰኝ ሆኖ ከጎኔ /2/

ጠላቴ እሳቱን እጥፍ ቢያነድም .

የማየው ነገር ተስፋ ባይሰጥም
ተስፋ ቢያስቆርጥም
የሱስ በራሱ ስዓት ይመጣል
ምን ይሳነዋል እሳቱን ያዛል
እኔንም ያወጣል

ስለኛ በደል ሞቶ የተነሳው
የአባቱን ሚስጥር ለእኛ የተረከው
ለአኛ የሰበከው
ባሕርም የብስም የሚታዘዙለት
ለግዛቱ ልክ ወሰን የሌለበት ገደብ የሌለበት

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top