ክብር ላምላክ በሰማይ ለሚኖር
ክብር ላምላክ በሰማይ ለሚኖር
በሰማይ ለእግዚአብሔር ምሥጋና ይሁን
በጎ ፍቃድ ላላቸው ሰላም ይሁን
ሁሉን የምትችል አብ ሰማያዊ ንጉሥ
ስለታላቁ ክብርህ ስምህ ይቀደስ
እናሞግስሃለን እንወድስሃለን
እናከብርሃለን እንሰግድልሃለን
የዓለምን ኃጢያት የምታጠፋ
የእግዚአብሔር በግ ሆይ ክብርህ ይስፋ
ትሁት ፀሎታችንን ተቀበለን
በአብ ቀኝ የምትቀመጥ ይቅር በለን
የአብ አንድ ልጅ የሆንክ አምላካችን
የሱስ ክርስቶስ ሆይ ይቅር በለን
የሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱስ አንተ ብቻ ነህ
ጌታ አንተ ብቻ ነህ ልዑል አንተ ብቻ ነህ
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በእግዚአብሔር
አብ ክብር ትኖራለህ
አሜን አሜን /6/
