ከፍ ብሎ ድምፄ ለአንተ ይድረስና
ወደ አንተ መቅደስ በክብር ልግባና
መስዋዕቴ ለአንተ ጥሩ ሽታን ይዞ
ከዙፋንህ ይድረስ አምላኬ ሆይ ቶሎ
ከተስማማ ምስጋናዬ
ከደረሰማ አምልኮዬ
መሻቴ ይህ ነው ፍላጎቴ
ክብርን ልስጥህ በዘመኔ /2/
የአፌን ቃል የአንደበቴን
ቤትህ ደርሶ መስዋዕቴ
ይመለሳል መልስን ይዞ
በረከትን ተቀብሎ /2/
ከቤትህ ሆኜ ካንተ ቦታ
በተቀደሰው በከፍታ
ዝቅ ማለቴን አነሣህው
ይኸው ምስጋናዬን ውሰደው / ተቀበለው
የኔ ምስጋና ከልቤ ፈልቆ
ከአንተ ሊደርስ ቅጥርን አልፎ
መክበርህንም እኔ ላክብረው
ጌታ አንተ ብቻ ተቀበለው /2/
