አሜን ማለት ለምደን ስራህንም አይተን
ይስጣችሁ ስንባል መስጠትህን አምነን
ይመስገን ስትባል መክበርህን ወደን
በተገኘው ሁሉ እኛ እያልን አሜን
አሜን /5/ /2/
እርግማን ተረስቶ ምርቃት ያለበት
ፈውስ የሚታይበት ታሞ የሚዳንበት
ፍፁም የተሞላ ሰላም ውሎ ማደር
ኣዲስ ልዩ ዘመን ያመጣል
እግዚአብሔር
ተደብቀን አንሄድም ወደምናመልከው
የእውነት ነው እርሱ የማንደብቀው
የሚያኮራ አገኘን ማፈሪያውን ትተን
ቀና ብለን ሄድን በርሱ ተመክትን
በሞኝነት ዘመን ተስፋ እንደጉም ስንዘግን
ላይገባው ስግደት ላያዋጣን ላይሆን
አንተማ የእውነት ነህ አንተማ የለህ አቻ
አንተማ ለዘላለም አንተማ አሜን
