አለማዬ አይደለም እራሴን መካቡ
ሞኝ እንደሚያስበው እንደሚያወራው
ሀያልም በሀይሉ ከቶ እንዳይመካ
የሁሉ መዝለቂያ እግዚአብሔር ነው ለካ 2
በእውቀት በጥበብ በሀይል
እንደሱ ከየት ይገኛል
የፍጥረታት ሁሉ መሪ
ብቻውን ዘላለም ነዋሪ
የሰው አይምሮ ውስን ነው
ብዙ አለ ፍፁም የማይችለው
እግዚአብሔር ሁሉን ይችላል
ተናግሮ እሱ ያደርጋል
በሠማይ ቢሆን በምድር
በጥልቁም ቢሆን በባህር
ማን አለ እንደርሱ ብርቱ
ጠንካራ ማይዝል ጉልበቱ
በቃሉ የፈጠራቸው
ፍጥረታት ከሱ ስር ናቸው
ዘወትር ክበር እያሉ
በቋንቋቸው ያዜማሉ
