ዙፋንህ በከበረ ቦታ
ማደሪያህ በብርሐን የሞላ
ልኡል ሆይ እጅግ ተአምረኛ
እግዚአብሔር ማን እንዳተ ለኛ 3
ባማረ መቅደስህ እጅግ በተዋበው
በክብር በግርማህ ደምቀህ ትታያለህ
ገናና ነህ አንተ በእውነት ልዩ ነህ
ሞገስህ አስፈሪ ሰፊ ነው መንግስትህ
የክብር መንፈስህ ቤትህን ሲሞላው
በእግርህ መረገጫ አንተ በቀደስከው
ታላቅነትህን ፍጥረተ ሁሉ ሲያውቀው
ምን ለአንተ ይሳናል ኢየሱስ ገናናው
ያአንተ ሐይል ሲገለጥ በኛ በደካሞች
ፀዳልህ ሲበራ ለኛ ለምሲኪኖች
በሰጠኸን ስልጣን በሐይል ስናዝበት
አከበርከን ጌታ እኛም አየንበት
