ወደኸኛል ጌታ ክብር ምስጋና ይገባሃል
ውለታህ ብዙ ነው ክብር ምስጋና ይገባሃል
ተመስገን እጅግ ወደኸኛል
ክበር ክበር ይገባሃል /2/
ከህፃንነቴ ጠብቀህ እስከዛሬ
ለቤትህ አቆምከኝ እንዳፈራ ፍሬ
በሰጠኸኝ ሰላም ስወጣ ስገባ
አለው ልዩ ደስታ ተመስገን አባባ
ለችግሬ ደራሽ እንደ ወላጅ አባት
የምትራራልኝ እንደ ወላጅ እናት
ፀሎቴን አድምጠህ በፊትህ ሳነባ
ቶሎ ቀረብከኝ ተመስገን አባባ
በስምህ ለመኖር ምንኛ ያስቀናል
የመንፈስ ደስታና ሕይወትን ያስገኛል
ቶሎ ለምስኪኑም እድል ሰጥተኸኛል
ተመስገን ልበልህ አስተደስተኸኛል
ክቡር ድንቅ ሥራህ ፍጥረትህን ሳይ
ረቂቅ ሚስጢርህ ከአእምሮ በላይ
እንዲህ ሆኖ አይቻለሁ እጅግ ያስደንቃል
የሚሳንህ የለም ክበር ይገባሃል
