አትፍራ ኣትደንግጥ እኔ አድንሃለሁ
በስምህ ጠርቼ ህዝቤ ብዬሃለሁ
የመከራ ብዛት ከቶ አይጥልህም
በእሳት ብትጣል አያቃጥልህም
ይህን ቃል የሰጠው
እግዚያብሔር እኮ ነው
ለኛ የሚያስበው
ሁልጊዜም መልካም ነው
በተናገረበት እንደበቱን ፀንቶ
እፎይ እንላለን ጉብኝቱ መጥቶ
አዋጅ አለን የደስታ የተስፋ ቃል
ለዚም ምድር የተሰጠ መፍትሄ አዘል
እግዚአብሔር ስለቃሉ ይፈፅመዋል
ሊባርከን ሊታደገን ይህን ተናግሮአል
ከፊት እየወጣሁ እመራችኋለሁ
ዛሬ አዲስ ነገር አሳያችኋለሁ
ደርቋል የተባለ ምንጭ ይፈልቅበታል
ህዝቤ ለዘላለም ጥማትን ይረሳል
በመረጥኩት ሰዓት ህዝቤ እመጣለሁ
መቼ አንጀቴ ችሎ ፍፁም ረሳሃለሁ
በእምነትህ ትጋ እየኝ ካንተ በላይ
በስጋ መፍትሔ የለም እኔነኝ ኤልሻዳይ
አዋጅ /2 አሀሀ /3 አሀሀ /2 አሀሀ
