ያየሁን አይቼ ነው ጌታን የተከተልኩት
ለዘለዓለም አሣልፌ እራሴን የሰጠሁት
ሰላሜ ልዩ ነው ስሆን ከኢየሱስ ጋራ
በምንም አልሰጋም እኔስ ፍፁም አልፈራ
ልቤን አሣረፍኩኝ በእርሱ ተማምኜ
እርሱን ተደገፍኩኝ ያዋጣኛል ብዬ
ከተማመንኩበት እርሱ አያሳፍርም
እኔስ አውቀዋለሁ እግዚአብሔር አይጥልም
አይጥልም/2/ ከታመኑበት ጌታ አይተውም
ፊቴን አላዞርም እኔስ ለአንድ አፍታ
የተሻለ የለም ከማመልከው ጌታ
እውነተኛ ወዳጅ ሽንገላ የለበት
እራሥን ቢሰጡት ልብን ቢጥሉለት
ታማኝ ነው /2/ አደራ አይበላም እሱ ፃድቅ ነው
አይነዋወጥም ስሬ መሰረቴ
ኢየሱስ ሆኖኛል ጠንካራ ምሽጌ
ወድጄ ፈቅጄ እርሱኑ ብያለሁ
የዘለአለሜ ነው ጌታን መርጫለሁ
ኢየሱስን ብያለሁ /2/ ከልብ ከነፍሴ አመልከዋለሁ
