ነገርን በሙሉ እያደላደለ
ሣናስብ ኣስቦ እያስተካከለ
ታሪክን ቀይሮ ታሪክን ይሰራል
የሚያስፈልገንን ከኛ በላይ ያውቃል
እግዚአብሔር እኮ ቀን አለው/2/
ሁለን ነገር ያስተካከለው
እግዚአብሔር ቀን አለው
ሃዘን ሲበረታ ድንገት ቀን ሲጨልም
ያ የመከራ እለት ለሊቱ ሲረዝም
እግዚኣብሔር ቀን አለው አስቦናልና
ለእውነተኛዋ ቀን ዋዜማ ነውና
ሀይል ያለው ሲበዛ ጠላት ሲበረታ
ብንደክም ብንወድቅ ክንዳችን ቢመታ
እግዚኣብሔር ቀን አለው ለሁሉም ይደርሳል
በሃዘናችን ላይ ደስታን ያወርሰናል
