1. እጅግ በሚያስፈራው ባስጨናቂው ሰአት
ጌታዬ ኢየሱስ ተኝቶ በታንኳ ውስጥ
ንፋሱ ቢነፍስም ወጀቡ ቢያይልም
ኢየሱስ ተነስቶ ሰርቶ አሳየን ታምር
አንተ ልትመለክ/ልትነግስ ይገባሃል ጌታ
ከሁሉ የበላይ የበላይ ነህና/2/
ሃሌሉያ የበላይ/3/
ጌታ ነው የበላይ
ሃሌሉያ የበላይ/3/
ኢየሱስ ነው የበላይ
2. አንተኑ ታምኜ ወጣሁኝ ልዋጋ
ምንም ታላቅ ቢሆን ጠላት የሚያሰጋ
አንተ ልትከብርብኝ መርጠኸኛልና
ጠላቴን አልፈራም አንተ አለኸኝና
3. ሁሉ የሞላው አምላክ አረ እንደርሱ ማነው
ከፍ ማለት ሲገባው ስለኔ ዝቅ ያለው
አመልከዋለሁኝ እስከመጨረሻው
እርሱ ነው አምላኬ ክብር የሚገባው
