ምህረቱ በዝቶ

124

ምህረቱ በዝቶ መከራዬ ድል ሆነ
በሱ መታመኔ እስራቴን ፈታ /2/

1. አጋጣሚ አይደለም በኔ ላይ የታየው
የጌታ ፍቃድ ነው ህይወቴን ያቆየው
የሚያስፈራ ዛቻ ጠላት ቢዝትብኝ
ያምላኬ ምህረቱ ፈጥኖ ደረሰልኝ

አዎ ምረቱ በዝቶ ነው
አዎ ጠላቴን ድል ነሳሁ
አዎ የጌታ ሆኛለሁ
አዎ ፍቅሩ ስለገዛኝ

አዎ ጉልበት ሆኖልኛል
ኣዎ ታግዬ እንዳሸንፍ
አዎ ትግስትን አደልከኝ
አዎ ፍቅርህ ሲበዛልኝ

ምህረቱ በዝቶ መከራዬ ድል ሆነ
በሱ መታመኔ እስራቴን ፈታ /2/

2. አወቅኩህ ጌታዬን ዛሬ በኔ ሰራ
ሞቴን አስወግዶ እስትፋሴን ሰራ
ጠላት ተስፋ ቁረጥ የጌታ ሆኛለሁ
ሃይልህ ተሽመድምዶ ከእጅህ አምልጫለሁ

አዎ እኔስ አምልጫለሁ
አዎ ምህረት በዝቶልኝ
አዎ መከራዬ ቀርቶ
አዎ ፍቅሩ በኔ አይሎ

አዎ የጠላቴ ወጥመድ
አዎ ከእግሬ ተፈታልኝ
አዎ የነፍሴ ፈጣሪ
አዎ አንተ ስትደርስልኝ

ምህረቱ በዝቶ መከራዬ ድል ሆነ
በሱ መታመኔ እስራቴን ፈታ /2/

3. ፍቅርህን አይቼ ምህረትን አስተዋልኩ
ባረኮትህ ሲበዛ ይህንን ተረዳሁ
ምንስ አነሰብኝ በዝቶልኝ እያየሁ
ሁሌም በምስጋና ፊቱ እቀርባለሁ

አዎ ምህረትህ ሲበዛ
አዎ ባርኮትህ ሲበዛ
አዎ ባይኔ አይቻለሁ
አዎ ከእኔ ስትጠጋ

አዎ ምህረትህ ሲበዛ
አዎ ፍቅርህ ሲበዛ
አዎ ልጅህን ፍለጋ
አዎ ከእኔ ስትጠጋ

ምህረቱ በዝቶ መከራዬ ድል ሆነ
በሱ መታመኔ እስራቴን ፈታ /2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top