አልችል ያልኩት ከኣቅሜ በላይ /2/
ለካስ አለ ጌታ ከሁሉ በላይ
ከሁሉ በላይ /4/
ለሰው የማይቻል ካቅም በላይ
ተራራ መሳይ በአይን ሲታይ
ለርሱ ለአምላኬ ይሄ ምንድነው
በቃሉ ብቻ አደላደለው
ለብዙ አመታት ያለቀስኩበት
ለእንቆቅልሼ መልስ ያጣሁበት
ምላሽ አግኝቷል ከላይ ከሰማይ
ሁሉን በሚችል ጌታ ኤልሻዳይ
ተደግፌአለሁ እኔስ በጌታ
በልቤ ሞልቶ ሰላም እፎይታ
የሚረዳልቃ አምላክ ስላለኝ
ለምንስ ልስጋ ምን አስጨነቀኝ
