አንድ ኣድርጎናል

125

አንድ አድርጎናል ኢየሱስ በደሙ
ከጠላት እስር ፈትቶን በሃይሉ
አያይዞናል ይታይ ፍቅራችን
አንገፋፋ እርስ በርሳችን

በመሽቀዳደም እንከባበር እንፈቃቀር
ማዶ ለማዶ መሆኑን ትተን /2/
በፍቅር እንኑር ኣንድ ሆነን ፀንተን
ሳንገፋፋ ሳንበታተን /2/

አንድ አድርጎናል የለም ልዩነት /2/
ኢየሱስ ያኔ የተሰዋ ዕለት የሞተልን ዕለት
ከተራራቅን እንጠጋጋ /2/
የአንድ አባት ልጆች ነን እኮ አንዘጋ /2/

እርሱን ጠጥተን እርሱን በልተናል /2/
በጌታ ኢየሱስ አንድ ወገን ሆነን ተያይዘናል
ዛሬም ኣንድ እንሁን እንደትላንቱ /2/
ፍቅራችን ይታይ በውጭ በቤቱ /2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top