ፍቅር ማለት ይኼ ነው

130

ከነዚህ ላንዱ ያደረከው
ለኔ እንዳደረከው መልካም ነው
ለምስኪኑ ላንዱ ያደረከው
ለኔ እንዳደረከው መልካም ነው
ፍቅር ማለት ይኼ ነው /2/
እየሱስ እንደተናገረው /2/

የፍቅር ትርጉሙን ተረዳ እወቀው
አጠገብህ ያለውን ወንድምህን ውደደው
በዓይንህ ያላየኸውን አምላክህን ብትወደው
ወንድምህን ጠልተህ ትርጉሙ ምንድነው

ፍቅር ማለት …….

ሲራብም መግበው ሲታረዝ አለብሰው
ሲጠማ አጠጥተህ ሲታሰርም ጐብኘው
ይኼ ነው ትርጉሙ ያንት ክርስትና
ዋጋው የከበረ የነፍስ ቅድስና

ፍቅር ማለት……

የከንቱ አይደለም የእኔ መልካም ሥራ
በላይ በሰማያት ስላለኝ ክፍያ

አለኝ ልዩ ስፍራ የተዘጋጀልኝ
እ/ር በቃሉ ያረጋገጠለኝ
እናንተ የአባቴ ብሩካን ኑ ትፈለጋላችሁ
ስፍራ የዘጋጀላችሁ
እናንተ የአባቴ ብሩካን ኑ ትፈለጋላችሁ
ቦታ የተዘጋጀላችሁ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top