ያልጠፋነው

132

ያልጠፋነው በእ/ር ምህረት ነው
እኛ ያልጠፋነው በእ/ር ምህረት ነው /2/

ምህረትን አድርጎ ስለኛ
ኃጢያት ሲጠላ ሆነን በደለኛ
በፍቅር ገዛን በምህረቱ
የሰው ልጅ ተፈታ እስራቱ
ምህረት አድርጎ እኛን አፍቅሮ
በእውነት ወዶን ውስጣችን አድሮ /4/

ኃጢያታችን በዝቶ ቢያዝንም
እ/ር ቸር ነው አይተወንም
ለወጠው ሞትን በልጁ ደም

ተሰዋ ስለኛ በዓለም
ምህረት አድርጎ እኛን አፍቅሮ
በእውነት ወዶን ውስጣችን አድሮ /4/

ለዚች ቀን ከርሱ ጋር ደርሰናል
ሸለቆ ዱሩን አልፈናል
ቀንም ሆነ ለሊት ሄደናል
በርሱ ግን ሁሉንም አልፈናል
ፍፁም ሳንሰማ ሳናይ መከራ
በለመለመው መስክ እየመራ
እየለወጠ ነገር በነገር
አደላደለን ኮራን በእ/ር /2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top