በምንም አልሰጋ ከቶ አልጨነቅም
አልሸነፍ እኔ በጠፊዋ ዓለም
ሁሌ አሸናፊ ነኝ እኔ በአባቴ
በደሙ የዋጀኝ ሆነልኝ /2/ ጉልበቴ /2/
ሃይልን በሚሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ /2/
አሸናፊነቴን ሁሌ እዘምራለሁ
ቃሉ ታማኝ ነው እመሰክራለሁ
እኔን ለመዋጋት አለም ብትነሳም
እኔን ለማሸነፍ ፈፅሞ አትችልም
ሁሉ ከርሱ በርሱ ለርሱ ሆኗልና
እሰዋለታለሁ የእርሱ /2/ ነኝና /2/
ሁሉን የምትገዛ አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ
የማይፈራህ ማነው ክብርህን ኦ ሲያይ
አህዛብ ይንበርከኩ በፊትህ ይውደቁ
የሃያላን አምላክ መሆንክን ይወቁ
ፈረስ ለጦርነት ማዘጋጀት ቢቻል
እ/ር ሲጨመር ሁሌም ድል ይሰጣል
በመስቀል ላይ ሞቶ ህይወት የሆነልኝ
ሽንፈትን አይደለም ድልን ነው /2/
ያስተማረኝ /2/
አ ሃያል /2/ አንተ /2/ ሃያል ነህ /6/
