አንተን ይዘን ወጥተን ይኸው አምሮብናል
አልከሰርንም በርግጥ ብዙ አትርፈናል
ምኞታችን ሰምሮ ባይናችን እያየን
ያደረክልንን እንመሰክራለን
ጌታ አንተን ታምኖ ያፈረ የለም
ሲሉ ሰምተናል ከጥንት ጀምረን
ዛሬ ግን አየን በህይወታችን /2/
ስትደግፈን ረዳታችን
ጥቂት አይደለም ለኛ ያረከው
አይቆጠርም ብዙ ብዙ ነው
ምስጋና እናብዛ ቢሆን ወሮታ
ሳንሰለች ጠዋትም ማታ /2/
ባንዱ አመስግነን ሳንጨርስ ገና
ሌላ ታምራት ደገምከውና
ምንለው አጣን እኛስ ደነቀን /2/
አንተን ሚመጥን ቃላትን አጥተን
ክንድህን አይተናል እናውቅሀለን
መልካምነትህን እናወራለን
ምስክሮችህ ሆነናል እኛ
ስለሆንክልን መተማመኛ
