አንዲት ቀንም ላልጨምር
በህይወቴ በእድሜዬ ላይ
እራሴን እጨርሳለው ወይ ስቃይ
ባዶዬ ሞላ አልሞላ ያኖረኝ እያስደነቀኝ
አምላክ አለኝ እኮ ዛሬ የሚያየኝ
ታዲያ ለምን እሰጋለሁ
ለምንድን እጨነቃለሁ
ስለእኔ እሱ ያውቃል
የሱስ ያስባል
በሰማይ ያሉ ወፎች በምድር ያሉ
አበቦች
በባህር በየብስ ያሉ ፍጥረቶች
እግዚአብሔር እያለ አንድም ቀን
አይኖሩም አጥተው
ይቸራቸዋል አይጎድልባቸው
ታዲያ ለምን እሰጋለው
ታዲያ ለምን እፈራለው
ነገን ለምን እፈራለው
ታዲያ ለምን ትሰጋላህ
ነገን ለምን ትፈራለህ
እግዚአብሔር እያለልህ!
ታዲያ ለምን ትሰጊያለሽ
ነገን ለምን ትፈርያለሽ
እግዚአብሔር እያለልሽ!
ለእኔማ ፍፁም ከእነርሱ አብልጦ ያስብልኛል(3)
ሁሉም በጊዜው ሆኖ አይቼው ያኔ ይገርመኛል
ቆርሶ ካዘጋጀልኝ ከዕድሌ ቀድሞ ካየልኝ
አንዱም አይቀር ለኔ ካለልኝ
ለምን በከንቱ ጭንቀት መንፈሴን አሳዝናለሁ
እ/ር አይጥለኝም አምናለሁ
