ስማይን ሳየው እገረማለሁ
ፍጥረትህን ሳይ /3/ እደነቃለሁ
አቤት እንዴት ውብ ያማረ /2/
እንዴት ውብ ያማረ ነው
ሰሪው አቤት ችሎታህ
አቤት እውቀትህ
አቤት ልቀትህ እግዚአብሔር
አሪው አትሳሳትም /3/ እግዚአብሔር
ጫካው ሸለቆ ደለል ገደሉ
የወንዞች ፍሰት ሲሞሉ
ወቅቶች ጠብቀው ሲፈራረቁ
አቤት ቅንብር ሲደንቁ
በቃልህ የቆመው ይህ ግዙፍ ሰማይ
ህይወት ነው ቀለሙ ሲታይ
ገዥ አደረከው ሁሉን ሊረታ
ዕውንም ያኖርከው ለታ
ብርሃኗን በቀን ሙቀትም ሰጥታ
ደግሞም ስትጨልም ለእርጋታ
ጨርሼ ነበር እራሴን ነቅንቄ
ፀሀይን ብቻ አድንቄ
ሁሉም ድንቅ ነው የእጅህ ፍጥረት
ቢመረምሩት በእውነት
ይህ ነው የገባኝ ደግሞም አልኩት
ልዩ ነው በእውነት እውቀትህ
እንዳንተ ያለ የለም /2/
እንዳንተ ያለ የለም /8/
ጌታ ነህ ከፍጥረት የበላይ
ንጉስ ነህ በፈጠርካቸው ላይ
ገዢ ነህ በፍቅር በኛ ላይ
ታላቅ ነህ በሰራሃቸው ላይ
ጌታ ነህ ከጌቶችም በላይ
ንጉስ ነህ በነገስታትም ላይ
ኃያል ነህ የኔ ጌታ የበላይ
