የጥበብ መጀመሪያ

138

ተነሳ አድሳ ተነሳ ከልሳ
የአንተን ክርስትና ዛሬ እንደገና
ተነሺ ከልሺ ተነሺ አድሺ
ያንቺን ክርስትና
እዪው ከቃሉ ፊት ለፊት ውደቂና

ስንማር መጀመሪያ እግዚአብሔር መፍራት ነው
ስናነብ መጀመሪያ እግዚአብሔር መፍራት ነው
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔር መፍራት ነው
የማወቅ አሀዱ አብ እግዚአብሔር መፍራት ነው

ከእርሱ በላይ ምንድነው
የምድሩማ ቀሪ ነው
እግዚአብሔር መፍራት በቂ ነው

ከንቱውን ነገር ስትነካካ
የዓለምን ልቧን ስታረካ
ኧረ እንዴት ጌታ ተዘነጋህ

ንቃበት ጠላት በእጁ አስገባህ

ተነሳ እንጂ በርታ በርታ
ማስተዋል አድርግ በእርጋታ
ልብህ ያሻውን ከምትሰራ
እግዚአብሔር ፍራ /2/
ተነሺ እንጂ በርቺ በርቺ
ማስተዋል መሪሽ ይሁን እንጂ
ልብሽ ያሻውን ከምትሰሪ
እግዚአብሔር ፍሪ /2/

በፍቅሩ ምህረት ስላኖረ
እግዚአብሔር ክብሩ ተደፈረ
አካሄድህን መዝንና
ከውሸት እራቅ ከስንፍና

የልቤን እረሱ ያውቃል ብለህ
በየዋህ ጥቅስህ ተሸንግለህ
እስከመቼ ነው መዝናናትህ
በክርስትና ወረቀትህ

ኑርለት ቃሉ እንደሚለው
ክርስቶስ ዛሬም ብርታትህ ነው
ትታደስ ነፍስህ ወስንላት
እንደጥምቀትህ ወራት

አትመልከተው በቸልታ
እግርህን ስብስብ አይሂድ መንታ
ኑርና እለፍ እንደቃሉ
ጽድቅ አይሆንህም ማስመሰሉ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top