ለእኔ ያደላል

137

እግዚአብሔር ያደረገው በእኔ ላይ ተአምር
ብዙ እኮ ነው ሰዎች ስሙኝ ልናገር /2/
ከአፈር ላይ አንስቶ እንዲህ ልዘምር
ኧረ እንዴት ወደደኝ ጌታ እግዚአብሔር /2/

ለእኔ /5/ ያደላል ለኔስ ያደላል /2/
ለኔስ /2/ አደላ ለኔስ አደላ /2/

የሆነልኝ አለ አዲስ /2/ ነገር
እግዚአብሔር ካዘዘኝ ይህን እንድናገር
ለኔ እማኝ እኔው ነኝ ለኔ እርሱ ልዩ ነው
ያየሁትን ሁሉ እመሰክራለሁ

የሆነልኝ አለ አዲስ /2/ ነገር
እግዚአብሔር ካዘዘኝ ይህን እንድናገር
ለኔ እማኝ እኔው ነኝ የእግዚአብሔር ህዝብ ይኸው
በሰውነቴ ላይ ያረገውን እየው

አልተለየኝም (ወ) …ስንቱን ሳጣው ፊቴ (ሴ)
አልተለየኝም (ወ)…ደርሶልኛል ስንቴ (ሴ)
አልተለየኝም (ወ)…ከኔ ለምዶ ሌላ (ሴ)
አልተለየኝም (ወ)…አላለኝም ችላ (ሴ)

አልተለየኝም (ሴ)…ጉድ አደባባይ (ወ)
አልተለየኝም (ሴ)…መኃል መንገዱ ላይ (ወ)
አልተለየኝም (ሴ)…አሳለፈኝ ማዶ (ወ)
አልተለየኝም (ሴ)…እንዴት ይጥላኝ ወዶ (ወ)

ለእኔ /5/ ያደላል ለኔስ ያደላል /2/
ለኔስ /2/ አደላ ለኔስ አደላ /2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top