እርሻም መብልን ባይሰጥ ከብቶችም ባይኖሩ
ወይንና በለስም ፍሬ ባያፈሩ
እኔ ግን በአምላኬ ሁሌ ደስለኛል
እድል ፈንታዬ ነህ ማን ይወስድብኛል /2/
አሃ…… አሃ ቢጎልም
አሃ…. አሃ ቢሞላም
አሃ…. አሃ አለውጥህም በሌላ
ዛሬም አመልክሃለሁ
ይኸው በፊትህ አለው
ካንተ ወዴት እሄዳለሁ
ሲሞላ ዘምሬ ሲጎድል ዝም አልልም
ከሁኔታዎች ጋር አንተ አትመዘንም
ፍፁም ጽድቅ ቅድስት እንደሆንክ አውቃለሁ
በስፍራዬ ሆኜ እጠብቅሃለሁ
እታመንሃለሁ
በጠላቴ ሃሳብ ጆሮዬን አልሰጥም
ለአለም ክብር ዝና ወድቄ አልሰግድም
ሥጋዬን በጥርሴ ነክሼ እኖራለሁ
እስከ ዘለዓለም አንተን አመልካለሁ
ለአንተ እገዛለሁ
