ለምን እንደወደድከኝ ለኔ ባይገባኝም
ለምን እንዳፈቀርከኝ ለኔ ባይገባቃኝ
ፍቅርህ ማርኮኛል አስሮኛል በቤትህ
ያዘምረኛል ሁሌም በፊትህ
ምንም ነገር የለኝም ፊትህ የሚያቆመኝ
በአንተ በፃድቁ የሚያስወድደኝ
ግን ስለበዛልኝ ከአንተ ምህረት
አለሁ እኖራለሁ ዘላለም በቤትህ
እኔ ራሴን ሳውቀው ላንተ ማልገባ
በክብር አየህኝ በቤት ስገባ
ክበርልኝ እንጂ እኔ ምን እላለሁ
በአንተ አይን ታይቼ ሞገስን ካገኘሁ
ሁሌ የሚያስደንቀኝ ያንተ ምህረት
ከውቅያኖስ የሠፋ የፍቅርህ ጥልቀት
እዘምረዋለሁ ዘወትር በፊትህ
እግዚያብሔር ልዮ ነው ፍቅር ነህ
እያልኩህ
