ለመለመች ቤቴ

147

ለመለመች / አማረባት/ ተውባለች ቤቴ
ኢየሱስ አንተን አስገብቼ

ሻካራ ጉዞዬን ጌታ አለስልሰሃል
መንገዴን እንዳልስት ጌታ መርተኸኛል
እጄን በእጅህ ይዘህ ደግፈኸኛል
ተመስገን ኢየሱስ ክብር ይገባል

አመፀኛውን ልቤን ጌታ ሰብረሃል
ፃድቁን ልብህን ተክተኸልኛል
ተንኮልና ጽድቅን ለይተኽልኛል
ተመስገን ኢየሱስ ክብር ይገባሃል

ምድረበዳውንም ጌታ አለመልመሃል
እባብና ጊንጡን እረግጠኽልኛል

እኔ ልሆን ባንተ ጉዞ ጀምሬአለሁ
ከእንግዲህ ኢየሱስ ልጅህ መጥቻለሁ

በሕይወቴ ሰላምና ፍቅርህ
ሕይወቴን ዳሰሳት አቃጠለህ እንደ እሳት
ጉብኝትህ በዝቶ አውቄ ለይቼ
ለመለመች ቤቴ አንተን አስገብቼ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top