ታላቅ የምስራች ትንቢት ተፈፅሟል
በዳዊት ከተማ አዳኙ ተወልዷል
ይኸውም ምልክት ይሆንላችኋል
ስለ ሰዎች ፍቅር በግርግም ተኝቷል
ታስረን የነበርነው በሐጥያት ሰንሰለት
ዛሬ ነፃ ወጣን በንጉሱ ልደት
ስለዚህ አትፍሩ አዳኛችን መጥቷል
የነቢያት ትንቢት በውነት ተፈፅሟል
ሐዘን በቃ እራቀ ደስታን ተክቶ
የአዳኝ መወለድ በአለም አስተጋብቶ
እልል እንበል እኛም ሐጥያታችን ጠፋ
በደስታ ለመኖር አግኝተናል ፋታ
ምድር ተናገሪ ደስታን አብስሪ
ታላቅ መሪ ኮከብ በስተ ምስራቅ አብሪ
ባለም ያስተጋባ የጌታችን መምጣት
ለኛ ስለሆነ ሊያወጣን ከሐጥያት
ወርቅ ይበርከትለት ለንጉስነቱ
እጣኑን እናድርግ ስለ አምላክነቱ
ክርቤውን እናቅርብ ስለ ሰውነቱ
ምስጋና ይድረሰው ስለ አዳኝነቱ
