1. ምድር ሰላም ሆነች እጅግ አማረባት
በከብቶች በረት ውስጥ ጌታ ወረደላት
ደስ ይበልሽ ማርያም ምስጋና ይድረስሽ
ድንግላዊ ሆነሽ አምላክን ወለድሽ
እልል እልል እልል /3/
ምስጋና ለማርያም ይገባል
2. ትንቢት ተፈፀመ የነቢያቶች
በዳዊት ከተማ ጌታን ወለደች
ከሴቶች የተለየሽ ማርያም ድንግሊቱ
ያንቺ ስም ሲጠራ ይወርዳል ምህረቱ
እልል እልል እልል /3/
ምስጋና ለማርያም ይገባል
3. ስምሽ የሚጣፍጥ ከማር ከወተት
ማርያም እመቤቴ ጌታን ወላዲት
ተንበርክኬ ልደር ልፀልይ ለክብርሽ
በአፌም ልዘምር ምስጋና ይድረስሽ
እልል እልል እልል /3/
ምስጋና ለማርያም ይገባል
