እርሱን እንድንበላ ፍቃዱ ለሆነው
እስከዚህም ድረስ ውርደት ለለበሰው
የማዘኑ ድንጋይ የቤክርስቲያን ራስ
ስሙ ብሩክ ይሁን ልኡል ጌታ ኢየሱስ
1. የአብርሐም ልጆች ወጡ ከባርነት
ምድረ በዳን ሊያልፋ በሙሴ መሪነት
መንገዳቸው ሁሉ ነበር በበረሐ
አይገኘም ነበር ምግብና ውሃ
እርሱን እንድንበላ ፍቃዱ ለሆነው
እስከዚህም ድረስ ውርደት ለለበሰው
የማዘኑ ድንጋይ የቤክርስቲያን ራስ
ስሙ ብሩክ ይሁን ልኡል ጌታ ኢየሱስ
2. በተአምራቱ ምግብ የመላእክቱን
ጌታ አበላቸው መና የተባለውን
ከአለት ድንጋይ ውሃን አፈለቀ
ታላቁ ስራውን ሰውን አስደነቀ
እርሱን እንድንበላ ፍቃዱ ለሆነው
እስከዚህም ድረስ ውርደት ለለበሰው
የማዘኑ ድንጋይ የቤክርስቲያን ራስ
ስሙ ብሩክ ይሁን ልኡል ጌታ ኢየሱስ
3. ሳሉ በበረሐ መናን እንዲበሉ
የተረፈ የለም ሞተዋል በሙሉ
ነገር ግን አሁንም በልተን እንዳንሞት
የሚያደርገን ምግብ አለልን በእውነት
እርሱን እንድንበላ ፍቃዱ ለሆነው
እስከዚህም ድረስ ውርደት ለለበሰው
የማዘኑ ድንጋይ የቤክርስቲያን ራስ
ስሙ ብሩክ ይሁን ልኡል ጌታ ኢየሱስ
4. ከላይ የወረደ የህይወት እንጀራ
ከእርሱ ከበላን ዘንድ ሞትን እንዳንፈራ
ከአምላክ የተሰጠ እውነተኛ መና
ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ይድረሰው ምስጋና
እርሱን እንድንበላ ፍቃዱ ለሆነው
እስከዚህም ድረስ ውርደት ለለበሰው
የማዘኑ ድንጋይ የቤክርስቲያን ራስ
ስሙ ብሩክ ይሁን ልኡል ጌታ ኢየሱስ
5. እኔን ከበላችሁ እኔን ከጠጣችሁ
ካስገባችሁኝም እኔን በውስጣችሁ
ሕይወት ብቻ እንጂ ሞት አታዩም ብሏል
ታላቅ የምስራች ለአለም አብስሯል
እርሱን እንድንበላ ፍቃዱ ለሆነው
እስከዚህም ድረስ ውርደት ለለበሰው
የማዘኑ ድንጋይ የቤክርስቲያን ራስ
ስሙ ብሩክ ይሁን ልኡል ጌታ ኢየሱስ
6. ህብስት ወደ ስጋ ቃል ሲናገር ቄስ
ወይኑን ደግሞ ወደ ደመ ክርስቶስ
በቅዳሴ ጊዜ እየተለወጠ
መንፈሳዊ ምግብ ለክርስቲያን ተሰጠ
እርሱን እንድንበላ ፍቃዱ ለሆነው
እስከዚህም ድረስ ውርደት ለለበሰው
የማዘኑ ድንጋይ የቤክርስቲያን ራስ
ስሙ ብሩክ ይሁን ልኡል ጌታ ኢየሱስ
