ለሚስጥረ ቁርባን

153

የሕይወት ምግብ ሚስጥረ ቁርባን
አንተን ስንቀበል ነፍሳችን ይዳን

ስጋና ደምህን እነሆ ብለኸን
ከቂምና ቅናት ከበቀል አዳንከን

ኦ የኢየሱስ ስጋ ኦ የኢየሱስ ደም
ከሐጥያት አነፃን ከነፍስም ህመም
እንስገድ በፊትህ በታላቅ ትህትና
አንተ ለኛ ብለህ እዚህ አለህና

ህፃናትን መስለን በፊትህ ስንቀርብ
የቁስልህ ምልክት በኛ ላይ ይነበብ
ስጋህና ደምህ የተቀደሰ ነው
አ አያል ኢየሱስ ምህረትህ ብዙ ነው

ልንቀበልህ ነው በፊትህ መጥተናል
የነፍሳችን ንጉስ ስጋህን ናፍቀናል
ደምህን ጠጥተን ከሞት እንድንድን
የአለም ንጉስ ሆይ ሕይወትን ሰጠኸን

በንስሐ ነጽተን ስንቀበልህ
የሐጥያትን መንፈስ ከኛ ለይተህ
በቅዱሱ ስጋህ እኛን አነፃኸን
የልብህን ፍቅር ግልፅ አደረክልን

ለሚስጥረ ቁርባን እንስገድ ሁላችን
እራሱን ለሰዋው ለመድሐኒታችን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top