ምን ያህል ጥልቅ ነው ለእኔ ያለህ ፍቅር
ነፍስን የሚያሰጥ ዋጋን የሚያስከፍል ኦ ኢየሱስ 14
እንዲህ የወደድከኝ ፍቅር የሚገባኝ
እረ እኔ ማን ነኝ /2/
ሆኜ ሳለሁ ያንተ አሳዳጅ
ጠላት እንጂ አይደለሁ ወዳጅ
በፍቅርህ የገዛኽኝ ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ
እራሴን ሣውቀው ማንነቴን /2/
የበዛ ነው ሓጥያቴ /2/
ይደንቀኛል ሁል ጊዜ
ያንተስ ፍቅር እየሱሴ
እስከሞት ድርስ ወደኽኛል
ራስህን ሰጥተህ አድነኸኛል
ከአዕምሮዬ ሰላይ ነው /2/
ያንተን ፍቅር አልገልጸውም /2/
ከምን ጋር ላወዳድረው
ጌታ ፍቅርህ ወደር የለው
የፍቅር ጥግ መጨረሻው
ባንተ ታየ መደምደሚያው
ከዚህ በላይ ፍቅር የለም /2/
ደግሞ አይታይ ለዘላለም /2/
