ለኔ ግን ጌታ ሆይ ውለታ በዛብኝ
የመሰቀሉ ፍቅር ዛሬም አሳሰበኝ
ይቅር በለኝና ልግባ ወደቤትህ
ከምስጋና በቀር /2/ ምን አለ የምክፍልህ
የሚጠቅመኝ መስሎኝ ብዙውን ደከምኩኝ
በዚህ አለም ደስታ በጣም ተታለልኩኝ
ስለዚህ ጌታ ሆይ አይዞህ በለኝና
ዛሬውኑ ጥራኝ /2/ ወደ አንተ ጐዳና
የሀጥያቴ ብዛት በጣሙን ከብዶኛል
ካንተ ግን ኢየሱሴ እርዳታ ያሻኛል
መስቀልን ልሸከም ይክበደኝ ሁል ጊዜ
ያላንተ ህይወቴ /2/ሆነብኝ ትካዜ
በጨለማው አለም ሳለው በመከራ
ደጉ ኢየሱስ ሆይ ልጅህን አደራ
ምህረትን ፈልጌ ፊትህ ቀርቢያለሁ
እኔስ ካንተ ሌላ /2/ ወዴት እሄዳለሁ
በድል አድራጊነት ከዚህ አለም እንዳልፍ
ምራኝ ከፊት ለፊት ሁነኝ የእኔ ድጋፍ
በመጨረሻው ቀን እዚያው በፍርድ ቦታ
አመሰግናለሁ/2/ ክብርህ ይስፋ ጌታ
