1. ከልቤ ምስጋና ከሚፈልቀው
እንደጅረት ሆኖ ከሚወርደው
ባሰናዳ ዛሬም ላንተ በዓል
አይበቃህም ይሄም ያንስብሃል /2/
ያንስሃል ጌታ ያንስሃል
ያንስሃል ውዴ ያንስሃል
ብዙ ምስጋና ሞልቶሐል
ያንስሃል ይሄ ምስጋና
ያንስሃል ጌታ አምልኮ
ይሄ ያንስሃል ምስጋና
አዎ ያንስሃል አምልኮ
ሲወዳደር ከሚገባህ ጋራ
እውነታ ነው ያንስሃል ሲወራ
ይሁን እንጂ እኔም ከማወደስ
ከቶ አልቆጥብም የልብን ከማድረስ
አላቆምም አንተን ከማወደስ
ምስጋናዬ ቤትህ ሞልቶ እስኪፈስ
2. ሰማይና ምድርን የሞላ ነው
ጌታ የአንተ ዙፋን ቃል እንዳለው
እድሜዬን ሰውቼ አቅሜን ባደርስ
ክብርህን አይሸፍን አይዳረስ
ያንስሃል ጌታ ያንስሃል
ያንስሃል ውዴ ያንስሃል
ብዙ ምስጋና ሞልቶሐል
ያንስሃል ይሄ ምስጋና
ያንስሃል ጌታ አምልኮ
ይሄ ያንስሃል ምስጋና
አዎ ያንስሃል አምልኮ
ሲወዳደር ከሚገባህ ጋራ
እውነታ ነው ያንስሃል ሲወራ
ይሁን እንጂ እኔም ከማወደስ
ከቶ አልቆጥብም የልብን ከማድረስ
አላቆምም አንተን ከማወደስ
ምስጋናዬ ቤትህ ሞልቶ እስኪፈስ
3. በንፁህ ልቦና በአንድ ሐሳብ ስር
በእውነተኛ አምልኮ ፍጥረት ቢያብር
የበዛው ምስጋና ያ ደስታህ ነው
በፊትህ ግን የሚሸት አንድ ጧፍ ነው /2/
ያንስሃል ጌታ ያንስሃል
ያንስሃል ውዴ ያንስሃል
ብዙ ምስጋና ሞልቶሐል
ያንስሃል ይሄ ምስጋና
ያንስሃል ጌታ አምልኮ
ይሄ ያንስሃል ምስጋና
አዎ ያንስሃል አምልኮ
ሲወዳደር ከሚገባህ ጋራ
እውነታ ነው ያንስሃል ሲወራ
ይሁን እንጂ እኔም ከማወደስ
ከቶ አልቆጥብም የልብን ከማድረስ
አላቆምም አንተን ከማወደስ
ምስጋናዬ ቤትህ ሞልቶ እስኪፈስ
