ቅድስት እናት ለዘለዓለም

-

ቅድስት እናት ለዘለዓለም
በልቤ ውስጥ እንዲታተም
የልጅሽ የኢየሱስ ህማም

የሐዘን እናት የእንባሽ ባህር
ቁማ ነበር እመስቀል ሥር
ተቸንክራ በፍቅር

ከባድ ሀዘን የተጫናት
ነፍሷን ቦታ የጠበባት
የሀዘን ሰይፍ የወጋት

ዋ የጭንቅሽ የእንባሽ ባህር
መጠን የለው ሥፍር ቁጥር
ቅድስት የአንድ አምላክ መንበር

ምን ይመስል ሀዘንሽ
ከመስቀሉ ያ ልጅሽ
ቁልቁል አንቺን ሲያይሽ

ማነው ከኛ እሷን አይቶ
ያንን ጭንቋን ተመልክቶ
እንባ የማይወጣው ከቶ

ማነው ከኛ ሳያዝንላት
ደፍሮ ጭንቋን የሚያይላት
ለዚያች ለአንድ አምላክ እናት

ስለሕዝቡ ኃጢያት
ኢየሱስን ሲገርፉት
ታይው ነበር በጭንቀት

ያንን ልጇን ወዳጇን
እመስቀል ላይ ድካሙን
ታየው ነበር ሞቱን

ካንቺ ጋር እንዳነባ
ያንቺ ሀዘን ልቤ ይግባ
ቅድስት የፍቅር አበባ

ልቤ እንደ እሳት እንዲቃጠል
ኢየሱስን በማገልገል
አማልጅን ቅድስት ድንግል

አንዱ ልጅሽ የሞተልኝ
ያለመጠን የወደደኝ
ሕማሙ ሕማም ይሁነኝ

ላልቅስ ላልቅስ ከአንቺ ጋር
ነፍሴ ሳለች ሳላባራ
ስለ ክርስቶስ መከራ

እመስቀል ስር በተገኘሁ
ከአንቺ ጋር ዋይ በነበርሁ
በደም እምባ በታጠብኩ

ከደናግል ሁሉ ድንግል
እንባ ይመጣል ስለአንቺ ስል
ስለ ልጅሽም መስቀል

ሸከሜ ይሁን የአምላክ ሞቱ
ደግሞ ርስቴ ሕማማቱ
ትዝታዬም ግርፋቱ

አበሳዬ ለዚያ ለእሣት
አሳልፎ እንዳይሰጣት
ድንግል ነፍሴን ታደጊያት

ነፍሴ ከሥጋ ስትወጣ
ኢየሱስ ሆይ ደጉን ዕጣ
ስለእናትህ እንዳላጣ

ስበሰብስ አፈር ስሆን
የነፍሴ ርስት ገነት ይሁን
ኢየሱስ ሆይ አደራህን

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top