ልውረድና ከከፍታዬ ላይ
ከፍ ላድርግህ አንተ ከብረህ ታይ
ዝቅ ብዬ ከከፍታዬ ላይ
አንተን ላሳይ ኢየሱስ ልቀህ ታይ
አንተ ከብረህ ታይ
ሁሌ ከብረህ ታይ
አምረህ ደምቀህ ታይ
ላንተ የሚገባው ክብር ሁሌም የብቻው ነው
እኔም ይህንን ብቻ ነው የማውቀው
ማለዳ ሌት አንተን ማክበር ክብሬ ነው
ስም የለኝ ስሜ ባንተ ነው መጠሪያ ማዕረጌ
ድምቀቴ ትምክህቴ ፍፁም ኩራቴ
ታሪኬ ዝርግፉ ጌጤ ውበቴ
እንደ 24ቱ ክቡር ሽማግሌዎች
በፊትህ እንደወደቁ ከእግሮችህ
ስእውነት እንዳመለኩህ ልጆችህ
ለክብርህ እንዳይገዛ እኔነቴ ማነው
የእኔ ነው ሁሉ የምለው ያንተ ነው
ከፍ በል ለዘለዓለም እላለሁ
ይበርቱ ዛሬም ይውደቁ መላ አካሎቼ
ከክብርህ በታች ልደፋ መጥቼ
በቤትህ ከዙፋንህ ስር ገብቼ
አይሻርም ዛሬ ይህ ነው የነፍሴ ውሳኔ
በክብሬ ባከብርህ ያዋጣል ለእኔ
ላለፍኩት ለሚመጣውም ዘመኔ
እንደ 24ቱ ክቡር ሽማግሌዎች
በፊትህ እንደወደቁ ከእግሮችህ
ስእውነት እንዳመለኩህ ልጆችህ
ለክብርህ እንዳይገዛ እኔነቴ ማነው
የእኔ ነው ሁሉ የምለው ያንተ ነው
ከፍ በል ለዘለዓለም እላለሁ
ጌትነት ለዘለዓለም ያንተ ነው
አድናቆት ለዘለዓለም ላንተ ነው
ታላቅ ነህ የዘለዓለም እውነት ነው
አምላኬ ታላቅነትህ ድንቅ ነው
ጌታዬ ታላቅነትህ ድንቅ ነው
ወዳጄ ታላቅነትህ ድንቅ ነው
