እውነተኛ እውነተኛ አምላክ

289

እውነተኛ እውነተኛ አምላክ
እውነተኛ የፍትህ አለቃ
እውነተኛ የወደቀን አይቶ
እውነተኛ ጓደኛ ማይከዳ
እውነተኛ እውነተኛ ወዳጅ
እውነተኛ የዘላለም አባት
እውነተኛ ጊዜ የማይሽረው
እውነተኛ ዝና የማይከዳ

የግሌ የራሴ የኔ ነው የምለው፡
ሰው የለኝ ጓደኛ ብዬ የምቆጥረው
አንድ ቀን ኢየሱስ በበሬ አለፈና
ታሪኬም በሙሉ በነበር ቀረና
ከሀብትም ከወዳጅ ከዘመድም በላይ
ስም አይቶ ማይከዳ ሆኖ የግሌ አዳኝ
ጉድፌና ኀጥያቴ ከላዬ ጠፋና
ከሰው እኩል ቆምኩኝ ሁሉም አለፈና
የግሌ የራሴ የእኔ ሆኗል ኢየሱስ ዛሬ /2/

አስተዋሽ አይዞህ ባይ ወዳጅ በሌለበት
ኀጥያተኛ ብሎ ሰው በከዳበት

ብቻዬን ሊወግሩ ነፍሴን ሊያጠፋት
አመንዝራ ብለው በፍርድ ሊያስቀጧት
ኢየሱስ ፊት ስቆም አትሞቺም ሲለኝ
ምህረቱ ሲነካኝ ክብሩ ሲዳስሰኝ
ሽክሜና ሀጥያቴም ከላዬ ጠፋና
ከሳሾቼም ጠፋ እኔም ተረፍኩና
ዛሬማ ደባሌም አጋሬም ኢየሱስ ሆኖልኛል /2/

ዛሬማ በቤቱ የክብር አክሊል ደፍቼ
ከሰው እኩል ሆንኩኝ ከናቁኝ ጓደኞቼ
ለተደረገልኝ ለዚህ ሁሉ ውለታ
ከአፈር ከትቢያ ላነሳኝ ድንቅ ጌታ
ሜልኮል ታላግጥ እንጂ በእኔ ምስጋና
እራቆቴን ቆሜ ብዘምር ባወራ
አይገደኝም ሀሜት የሰው አሉባልታ
አውቀዋለሁና የዋለልኝን ውለታ
ምስጋና ለስሙ ለክብሩ አቀርባለሁ ዛሬ /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top