መልካም ስራችን

107

መልካም ስራችን ታይቶ እንዲከበር የሰማይ አባታችን
ብርሃናችን በሰው ፊት ይብራ ይታይ የእውነት ፍቅራችን

ታላቅ ተልእኮ አለን የምድር ጨው ተብለን
ከዳር እስከዳር ሄደን በመልካም ምሳሌ ሆነን
ግን ነፍሳት ሲጠብቁ ወንጌልን ሲናፍቁ
ቀድሞ የኛ ህይወት ጣእም ካጣ ማን ወደ ኢየሱስ ሊመጣ

ከመቅረዙ ስፍራችን ደምቆ ይብራ ጧፋችን
ምድር ይድረሳት ጠርቶ ህይወታችን ተለይቶ
ነገስታት ይማረኩ አማልክት ይንበርከኩ
ወንጌሉን ብቻ ይወቁ በውሎችን ጌታን አይናቁ

ይጥራ ጽኑ ፍቅራችን ንግግር ሰላማችን
ለሚያምኑት የህይወት ሽታ ልንሆን ጠርቶናል ጌታ
ደግሞም የወንጌል ስራ የሁላችን አደራ
ይግለጥ መክሊታችን አይሰወር መብራታችን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top