በኃጢያት አረንቋ ጠፍተን ስንዳክር
መንገዱ ተረስቶን ስንደናበር
ከፍጥረታት ሁሉ ወዶ የመረጠሽ ለኛስ
አለኝታችን መሸሽጊያችን ነሽ
ኃጢአታችን በዝቶ አንገት ሲያስደፋን
በጌታ አደባባይ መቆም ሲያቅተን
ጥላና ከላላ እንድትሆኝልን
ማርያም ሆይ አንቺን እንለምናለን
ህሊናችን ሲራብ የገነት ወይን
ሊያድርብሽ አስቦ ጌታ ሊምረን
ለኢያቄም ለሐና አንቺን ባርኮልን
መለኮት በስጋሽ ሥጋን ነሳልን
ሁል ጊዜ ማርያም ሆይ እንልሻለን
ልጅሽ እንዲረዳን እንዲራራልን አንቺን
ተጠግተን ተማፅነን
በስምሽ ለምነን ምንም አላጣን
